መጽሐፍ " አንቺ መዶሻዬና የጦር መሣሪያዬ ነሽ፤ በአንቺ አሕዛብን እሰባብራለሁ፤ በአንቺም መንግሥታትን አጠፋለሁ፤ "
(ትንቢተ ኤርምያስ 51:20፤) የሚላት ሩሲያ ትመስለኛለች።
ሩሲያ በአውሮፓ እና እስያ አህጉሮች ውስጥ የምትገኝ አገር ናት። በ17,075,200 ካሬ ኪ.ሜ. ከዓለም በመሬት ስፋት አንደኛ ስትሆን በሕዝብ ብዛትም ከዓለም ስምንተኛ ናት። ሩስያ ከኖርዌ፣ ፊንላንድ፣ ኤስቶኒያ፣ ሌትላንድ (ላቲቪያ)፣ ሊትዌኒያ፣ ፖላንድ፣ ቤላሩስ፣ ዩክሬን፣ ጆርጂያ፣ አዘርባይጃን፣ ካዛኪስታን፣ የቻይና ሕዝባዊ ሬፑብሊክ፣ ሞንጎሊያ እና ሰሜን ኮሪያ ጋር ድንበር አላት።
በምስራቃዊ አውሮፓ ክፍል የሚኖሩ የስላቭ ህብረተሰብ ወደ አሁኗ ሩስያ ከሶስት እስከ ስምንተኛው ክፍል ዘመን ተሰደዱ። ኬይቫን ረስ የሩስያ ህዝብ ማንነት እንዲኖሮ በማድረግ ከ9ኛው ክፍለ ዘመን ጀምሮ የነበረ ትልቅ ግዛት ነው። በተጨማሪም፣ የሩስያ ኦርቶዶክስ መነሳት ትልቅ ሚና ተጫውቷል። በ988 ዓም፣ ክርስትና ከቢዛንታይ ወደ ሩስያ ተስፋፋ። ልክ የረስ ስልጣን በሞንጎል ወረራ ሲዳከም፣ ምስራቃዊ ክፍሏ በልዕልና እስከ 13ተኛው ክፍለ ዘመን ይመራ ነበር። እስከ 18ተኛው ክፍለ ዘመን ድረስ፣ ምዕራባዊው ግዛት በፍጥነት ድንበሯን ወደ ምስራቅ በማስፋፋት የሩስያ ኢምፓየር መመረት ችላለች። በ1917 የተነሳው የሩስያ አብዮት የመንግስቱን ስርአት ወደ ሶሻሊስት በመቀየር የሶቬት ህብረትን በ1922 አቋቋመች። ሰፊውን የምስራቃዊ አውሮፓና መካከለኛ እስያ ክፍልን የሚይዘው የሶቬት ህብረት በሁለተኛው የአለም ጦርነት አክሲስ ሀያላንን በመዋጋት ጎልህ ሚና ነበራት። ነገር ግን ከጆሴፍ ስታንሊን አመራር ጀምሮ፣ የሶቬት ህብረት አምባገነናዊ እየሆነ ሄደ። ብዙ ቤት ክርስቲያኖች ወደሙ፣ ብዙ ሰዎች ተገደሉ፣ ብዙ አይሁዶች ከቀያቸው ተፈናቀሉ። የሶቬት ህብረት ከአሜሪካ ጋር የቀዝቃዛውን ጦርነት ስታስጀምር ብዙ ደባና ጭካኔ አድርሳለች። ለምሳሌ፣ የቬትናም ጦርነት ላይ ከአሜሪካ ጋር የውክልና ጦርነት በማድረግ ሰብዕዊ መብት ጥሳለች። በተቃራኒው ሶቬት በሳይንስና ቴክኖሎጂ እጅግ በጣም መበልፀግ የጀመረችበት ጊዜ ነበር። በማርክሲዝ ሌኒንዝም አብዮት የተሞላችው ሶቬት ህብረት በ1991 በህዝበ ውሳኔ ልትፈርስ ችላለች። ሩስያ በ1993 መንግስቷን ወደ ፌድራል ልትቀይር ችላለች፤ እስካሁንም ትመራለች።
ሩስያ ሀያላን ሀገር ናት። በተጨማሪም በጦርና በማዕድን የምትታወቅ ናት። ሩስያ ሀያልና ከመሆኗም በላይ ከምዕራብያውያን አካላት ጋር እልህ አስጨራሽ ፉክክር ና ጠላትነት ከነበራት ከ200 አመታት በፊት ነበረ። የሩስያ አመለካከት ከሌሎች ምዕራባዊ ሀገራት በአንፃሩ በመለየቱ፣ በተጨማሪም ሩስያ ጣልቃገብና ተፅዕኖ ፈጣሪ ስለማትፈልግ በምዕራብያውያን ህብረተሰብ እጅግ የምትጠላ ሀገር ናት። ሩስያ የኒው ወርልድ ኦርደር የምዕራባዊ አምባገነናዊ የአለም መንግስትን ትፃረራለች፤ እንዲሁም የምዕራብያውያን ሴራ ለማገለጥ የምትጥር ብቸኛ ሀገር ናት። የሩስያ ህዝቦች ከምዕራብያውያን የሚለዩት የኦርቶዶክስ ክርስትና ሀይማኖት በብዛት ያየለና ጥቂት ኢአማኞች የሀይማኖትን ነፃነት ና አርበኝነትን ይደግፋሉ። ይህንንም በመመልከት ምዕራብያውያን በሩስያ ላይ ትልቅ ቁጣ አንስቷል። ስለሆነም፣ ፕሮፓጋንዳን በመጠቀም፣ የምዕራብያውያን ሀገራት የሩስያን ስም ለማጠልሸትና ኦርቶዶክስ ክርስትናን በሀገሪቷ በማጥፋት ትልቅ እቅድ እየሰሩበት ይገኛሉ። በቅርቡም ሩስያ የክሪምያና ዶንባስ ግዛት በማጠቃለል፣ ከዩክሬን ጋር በተደጋጋሚ ጦርነት ውስጥ ገብቷል። ዩክሬን፣ በምዕራብያውያን ኔቶ በመደገፍ ሩስያን እስካሁን ድረስ እየተፋለመቻት ነው። በብዙ ሀያስያን እይታ የሩስያና ዩክሬን ውጊያ "ሶስተኛ የአለም ጦርነት" ወይም "ሁለተኛ ቀዝቃዛ ጦርነት" ይከሰታል ይላሉ። የኔቶም እንቅስቃሴም በዩክሬን ላይ የውክልና ጦርነት የሚያድረግ ነው።
Comments
Post a Comment