" የአማልክት አምላክ ፥ የአጋዕዝት ጌታ ፥ የልዑላን ልዑል! " ነው። እርሱ " የእሳት መጎናጸፊያ የተጎናጸፈ ፥ በነደ እሳት ያጌጠ ፥ የተጌጠ ፥ ዙፋኑ፦ የእሳት ፥ መመላለሻው፦ " በዐይን በማይታይ ፥ በእጅ በማይጨበጥ! " ፦ አየር ፥ ጠፈሩ፦ ሰማይ ፥ መንኮራኩሩ፦ደመና ፥ ጎዳናው፦ የባሕር ማዕበል ነው።
#ዳዊት_ፀሐይ #እንኳን_አደረሳችሁ " ነቢዬ እግዚአብሔር ቅዱስ ዳንኤል! "፦ " ዙፋኖችም እስኪዘረጉ ድረስ አየሁ ፥ በዘመናት የሸመገለውም ተቀመጠ። ይለዋል " እግዚአብሔር አብን! " ነው። ይህን ጉዳይ " ቅዱስ ጎርጎርዮስ! ፦ " አምላክነ ዘእንበለ ጥንት ፥ ወመድኃኒነ ዘእንበለ ተፍጻሜት! " ፥ " ጥንት የሌለው አምላክ ፥ ፍጻሜ የሌለው መድኃኒት! " እያለ ይጠቅሰዋል። " እሱ ፥ እራሱ፦ " እግዚአብሔር አብ " <<ያለና የሚኖር>> እኔ ነኝ! " (ኦሪት ዘጸአት 3:14፤) እንዲል " ሕልፈት ፥ ውላጤ! " የማይስማማው ፥ " ጉም ፥ ደመና! " የማይጋርደው ፥ " እሳት ፥ ባሕር! " የማይከለክለው ፥ " በዚህ አለ ፥ በዚህ የለም! " የማይባል ፥ " ለዘመኑ ሕልፈት ፥ ለግዛቱ ወሰን! " የሌለው አምላክ ነው። እና ለዘመኑ " ጥንት! " ተብሎ ስለ ማይነገርለት " ነቢዬ እግዚአብሔር ቅዱስ ዳንኤል! " ፥ " በዘመናት የሸመገለው! " አለው። ምንም እንኳ ፍጥረት የፈጠረ እርሱ ቢሆንም እርሱ፦ ብርሃናት ሳይመላለሱ ፥ ነፋሳት ሳይነፍሱ ፥ ማያት ( ወንዞች ) ሳይፈሱ ፥ ቀን እና ሌሊት ፥ ክረምት እና በጋ ሳይፈራረቁ እሱ ነበረ። ይሄን ሲያይ " በዘመናት የሸመገለው! " አለው። እንደ ገናም ነቢዩ " ልብሱም እንደ በረዶ ነጭ፥ የራሱም ጠጕር እንደ ጥሩ ጥጥ ነበረ፤ ዙፋኑም የእሳት ነበልባል ነበረ፥ መንኰራኵሮቹም የሚነድድ እሳት ነበሩ። "(ትንቢተ ዳንኤል 7:9፤) ይለዋል። ቅዱስ ቄ...