Skip to main content

" የአማልክት አምላክ ፥ የአጋዕዝት ጌታ ፥ የልዑላን ልዑል! " ነው። እርሱ " የእሳት መጎናጸፊያ የተጎናጸፈ ፥ በነደ እሳት ያጌጠ ፥ የተጌጠ ፥ ዙፋኑ፦ የእሳት ፥ መመላለሻው፦ " በዐይን በማይታይ ፥ በእጅ በማይጨበጥ! " ፦ አየር ፥ ጠፈሩ፦ ሰማይ ፥ መንኮራኩሩ፦ደመና ፥ ጎዳናው፦ የባሕር ማዕበል ነው።


 #ዳዊት_ፀሐይ


#እንኳን_አደረሳችሁ


" ነቢዬ እግዚአብሔር ቅዱስ ዳንኤል! "፦ " ዙፋኖችም እስኪዘረጉ ድረስ አየሁ ፥ በዘመናት የሸመገለውም ተቀመጠ። ይለዋል " እግዚአብሔር አብን! " ነው። ይህን ጉዳይ " ቅዱስ ጎርጎርዮስ! ፦ " አምላክነ ዘእንበለ ጥንት ፥ ወመድኃኒነ ዘእንበለ ተፍጻሜት! " ፥ " ጥንት የሌለው አምላክ ፥ ፍጻሜ የሌለው መድኃኒት! " እያለ ይጠቅሰዋል። " እሱ ፥ እራሱ፦ " እግዚአብሔር አብ " <<ያለና የሚኖር>> እኔ ነኝ! " (ኦሪት ዘጸአት 3:14፤) እንዲል " ሕልፈት ፥ ውላጤ! " የማይስማማው ፥  " ጉም ፥ ደመና! " የማይጋርደው ፥ " እሳት ፥ ባሕር! " የማይከለክለው ፥ " በዚህ አለ ፥ በዚህ የለም! " የማይባል ፥ " ለዘመኑ ሕልፈት ፥ ለግዛቱ ወሰን! " የሌለው አምላክ ነው። እና ለዘመኑ " ጥንት! " ተብሎ ስለ ማይነገርለት " ነቢዬ እግዚአብሔር ቅዱስ ዳንኤል! " ፥ " በዘመናት የሸመገለው! " አለው። 

ምንም እንኳ ፍጥረት የፈጠረ እርሱ ቢሆንም እርሱ፦ ብርሃናት ሳይመላለሱ ፥ ነፋሳት ሳይነፍሱ ፥ ማያት ( ወንዞች ) ሳይፈሱ ፥ ቀን እና ሌሊት ፥ ክረምት እና በጋ ሳይፈራረቁ እሱ ነበረ። ይሄን ሲያይ " በዘመናት የሸመገለው! " አለው። 

እንደ ገናም ነቢዩ " ልብሱም እንደ በረዶ ነጭ፥ የራሱም ጠጕር እንደ ጥሩ ጥጥ ነበረ፤ ዙፋኑም የእሳት ነበልባል ነበረ፥ መንኰራኵሮቹም የሚነድድ እሳት ነበሩ። "(ትንቢተ ዳንኤል 7:9፤) ይለዋል። ቅዱስ ቄርሎስ ደግሞ ይሄን ጉዳይ 

እርሱ፦ " የአማልክት አምላክ ፥ የአጋዕዝት ጌታ ፥ የልዑላን ልዑል! " ነው። እርሱ " የእሳት መጎናጸፊያ የተጎናጸፈ ፥ በነደ እሳት ያጌጠ ፥ የተጌጠ ፥ ዙፋኑ፦ የእሳት ፥ መመላለሻው፦ " በዐይን በማይታይ ፥ በእጅ በማይጨበጥ! " ፦ አየር  ፥ ጠፈሩ፦ ሰማይ ፥ መንኮራኩሩ፦ደመና ፥ ጎዳናው፦ የባሕር ማዕበል ነው። ብሎ ያብራራዋል።

እንደ ገናም ነቢዩ " የእሳትም ፈሳሽ ከፊቱ ይፈልቅና ይወጣ ነበር፤ ሺህ ጊዜ ሺህ ያገለግሉት ነበር፥ እልፍ አእላፋትም በፊቱ ቆመው ነበር፤ ፍርድም ሆነ፥ መጻሕፍትም ተገለጡ።  (ትንቢተ ዳንኤል 7:10፤) ይለዋል።

" ሺህ ጊዜ ሺህ ያገለግሉት ነበር ፥ እልፍ አእላፋትም በፊቱ ቆመው ነበር ! " ሲል " መላእክትን! " ነው። " ሺህ ጊዜ ሺህ! " ሲል ስለ ብዛታቸው ሲሆን አንድም ስለ " ሕዋሳቸው! " ነው። ምንም እንኳ መላእክት እረቂቅ ቢሆኑም አካል አለቸው። አካል ስላላቸው ሕዋስ አላቸወ። በአላቸው ሕዋሳት ሁሉ እግዚአብሔር አብን  ያመሰግኑታል።

ይሄንም ጉዳይ " እንደ እንግዳ ደራሽ ፥ እንደ ውኃ ፈሳሽ! " አዲስ ነገር እንዳይመስል " ነቢዬ እግዚአብሔር ቅዱስ ሕዝቅኤል! " በአላቸው ሕዋሳት ሁሉ እንዴት? እንደ ሚያመሰግኑት " ክንፋቸው ሲበር ድምጽ አለው! " (ትንቢተ ሕዝቅኤል 1:24፤) ይላዋል። ሊቁም " ከመ ቃልከ ሻደይ! " ፥ " ሻደይ ፥ ሻደይ! " ይላል። " ሻደይ! "  ማለት ፦" ኃይል ፥ ጽኑዕ ፥ ዐዚዝ ፥ ክቡር ፥ አኀዜ ኩሉ ፥ ከሀሌ ኩሉ! " ማለት ነው። ብሎ ተርጉሞታል። በዕብራይስጥ እጅግ የከበረ ፥ የገነነ ስም ነው። ሙት የሚያነሳ ፥ ለምጻም የሚያነጻ ፥ አጋንትን የሚያርቅ ፥ የሚያወጣ " ቃል! " ነው።

እንዴውም በሀገራችን " አሸንድዬ ፥ ሻደይ ፥ አሸንዳ! " ከዚህ የወጣ ይመስላል ጥናት ይጠይቃል።

ከዛ ነቢዩ " ፍርድም ሆነ፥ መጻሕፍትም ተገለጡ። (ትንቢተ ዳንኤል 7:10፤) ይለዋል። ቅዱስ ዮሐንስም በራእዩ  " መጽሐፍም ተከፈተ እርሱም የሕይወት መጽሐፍ ነው! "(የዮሐንስ ራእይ 20:12፤) ይለዋል። ቅዱስ ሙሴ "  እግዚአብሔር አምላክም ሰውን ከምድር አፈር አበጀው፤ በአፍንጫውም የሕይወት እስትንፋስን እፍ አለበት፤ ሰውም ሕያው ነፍስ ያለው ሆነ። " (ኦሪት ዘፍጥረት 2:7፤) እንዲል ያ " የሕይወት መጽሐፍ! " የተባለ " መንፈስ ቅዱስ! " ነው። " በሕይወትም መጽሐፍ ተጽፎ ያልተገኘው ማንኛውም በእሳት ባሕር ውስጥ ተጣለ። " (የዮሐንስ ራእይ 20:15፤) እንዲል " መንፈስ ቅዱስን! " ከአብ የሠረጸ ያላለ " እድል ፈንታው ፥ ጽዋ ተርታው! " በገሃነም እሳት ነው።

ከዛም ነቢዩ " የሰው ልጅ የሚመስል ከሰማይ ደመናት ጋር መጣ በዘመናት ወደ ሸመገለውም ደረሰ፤ ወደ ፊቱም አቀረቡት። " (ትንቢተ ዳንኤል 7:13፤) ይለዋል።

" ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ! " ነው።

 የሰው ልጅ የሚመስል አለው፦ " በሥጋ ማርያም ፥ በክበበ ትብስእት! " መገለጥኑን ሲናገር ነው። " ከሰማይ ደመናት ጋር መጣ! " አለው በክብር ፥ በይባቤ ማረጉን ሲያይ ነው። በዘመናት ወደ ሸመገለውም ደረሰ፤ አለ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ " እርሱም የክብሩ መንጸባረቅና የባሕርዩ ምሳሌ ሆኖ፥ ሁሉን በስልጣኑ ቃል እየደገፈ፥ ኃጢአታችንን በራሱ ካነጻ በኋላ በሰማያት በግርማው ቀኝ ተቀመጠ፤" (ወደ ዕብራውያን 1:3፤) እንዲል እርሱ ፦ " ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ( እግዚአብሔር ወልድ! ) " ፥ " እግዚአብሔር አብን " በመልክ የሚመስለው ፥ በባሕርይ የሚተካከለው! " ሁኖ " ብርሃነ ፀሐይ ከዓይን ጋር ተዋሕዶ ክበቡን እንዲያስታውቅ ፥ እሱም ሥጋን ተዋሕዶ " እኔን ያየ አብን አየ! " ፥ " እኔ እና አብ አንድ ነን! " ፥ " ከኔ በቀር ወደ አብ የሚወጣ የለም! " እያለ አባቱን አስታወቃቸው።  " ሁሉን በስልጣኑ ቃል እየደገፈ ፦ ብርሃናትን እያመላለሰ ፥ ነፋሳትን እያነፈሰ ፥ ቀን እና ለሊትን ፥ ክረምት እና በጋ! " እያፈራረቀ ፥ የቡሉይ ኪዳን ሊቀ ካህን " የሚያነጻ እሱ ፥ የሚነጹት ሕዝቡ ፥ እራሱ ፥ የሚያነጻ! " ደም ነው።  ደሙ ልዩ ፥ ልዩ ነው። ደመ ላም ፥ ደመ በግ ፥ ደመ ጠሊ ( የፍየል ) ነው። እሱ ግን " የሚያነጻ እርሱ ፥ እራሳችን ፥ የምንነጻ እኛ ፥ ሕዋሳችን ፥ የሚያነጻን ደሙ! " ሁኖ " ኃጢአታችንን በራሱ ካነጻ በኋላ " በሰማያት በግርማው ቀኝ! " ተቀመጠ። " ቅዱስ ዮሐንስ አፈፈ ወርቅ! " ፦ እሰመ ነቢር በዕሪና የኤምር ኅበ ተዋሕዶቶሙ በክብር " ይላል " በሰማያት! " ሲል ቦታ ወስኖለት አይደለም። " በክብር መተካከሉን! " ሲያሳይ ነው።

Comments