Skip to main content

Posts

Showing posts from April, 2022

የመስቀሉ ነገር.....Dawit tsehay

  የመስቀሉ ነገር..... #ዳዊት_ፀሐይ ( የፀሐፊው መብቱ የተጠበቀ ነው። ) 《 ዐይን ያላየው ፥     ጀሮ ያልሰማው ፥     በሰው ልቡና ያልታሰበ ፥      " እኛ ልንከብርበት እግዚአብሔር ያከናወነው ፥ ዓለም ሳይፈጠር ያነጸው ፥  ያጸናው《 ነገረ መስቀል! 》ነው::   (1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 2: 7-10 )  " የምናገረው ነገር! + የማስተምረው ትምርት! " የሰውነት ልባምነት በማታለል አይደለም::  መንፈስ ቅዱስ ባደረብኝ " ቋንቋ! " በመናገር! + መንፈስ ቅዱስ በገለጠው " ምሥጢር! " በመግለጥ ነው::   《 ድዊ በመፈወስ! +       ለምጻም በማንጻት! +       ጋኔን በማውጣት! +        ሙት በማስነሳት! 》ነው::  " ጠቢባን! " ነን ለሚሉ ሰዎች " ጥበብን! "  እነግራቸዋለሁ:: የምነግራቸው " ጥበብ! "  የዚህ ዓለም ነገስታት! + የዚህ ዓለም ፈላስፎች! የሚያዉቁትን " ጥበብ! "  አይደለም::  የዚህ ዓለም ነገስታት! + የዚህ ዓለም ፈላስፎች! የላወቁትን  《 ከእግዚአብሔር የተገኘውን እውነተኛ ጥበብን ነው::  》  ይህን《 " ጥበብ! " አውቀውትስ ቢሆን ኑሮ! + የክብርን ጌታ! + ባልሰቀሉት ነበር!》  ስለዚህም ነገር " ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ! "   《 አባት ሆይ፥ የሰማይና የምድር ጌታ፥ ይህን " ጥበብ! " ከጥበበኞች!  እና ከአስተዋዮች! + ጠበበኛ! እና አስተዋይ!  " ነን! " ከሚሉት " ከጻሕፍተ ሰፈርሳዊ...

በመገረፉ ቁስል ተፈወሳችሁ። Dawit tsehay

  " በመገረፉ ቁስል ተፈወሳችሁ። እንደ በጎች ትቅበዘበዙ ነበርና፥ አሁን ግን ወደ ነፍሳችሁ እረኛና ጠባቂ ተመልሳችኋል። " (1ኛ የጴጥሮስ መልእክት 2:25፤) #ዳዊት_ፀሐይ ( የፀሐፊው መብቱ የተጠበቀ ነው። ) " እንደ በጎች ትቅበዘበዙ ነበር! " አለ 《 እንደ ታመመ በግ! 》 ማለት ነው:: የተመመን በግ ከመጋው ለይተው! +  ከደረቅ ቦታ አስረው! +  ደረቅ ሣር! + ጥሩ ውኃ ይመግቡታል! + ሲድን ታቅፈው ቀስደው ከመንጋው ይጨምሩታል:: " እንደ ታመመ በግ! "  አለ 《 " ታሞ! "  የነበረ ገነትን ያህል ቦታ! +  እግዚአብሔርን ያህል ጌታ!  አጦ የነበረ " አዳም! " ነው:: " 》" ከመንጋው እንደ መለየት! " 《 አዳምም ከማኅበረ መላእክት ተለይቷል! 》"  ከደረቅ ቦታ አስረው! + ደረቅ ሣር! + ጥሩ ውኃ!  እንዲመግቡት! " 《  ነፍሶሙሰ ለጻድቃን ውስተ እደ እግዚአብሔር ወኢለከፎሙ ላህበ ሥቃይ ወኢምንትኒ! 》 እንዲል《 5500 ዘመን በእደ እግዚአብሔር ሲጠበቅ ኑሯል! 》" ሲድን ወስደው ከመንጋው እንዲጨምሩት! " 《 ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስም ባሕርዩን በሕርይ አድርጎ! + ጽንዓ ነፍስን ሰጥቶ አድኖታል! 》  " ክብር ምሥጋና ለአግዚአብሔር ይሁን። "

" ዕለተ ዐርብ፦ እግዚአብሔር የሠራት ቀን ይቺ ናት " Dawit tsehay

 " ዕለተ ዐርብ፦ እግዚአብሔር የሠራት ቀን ይቺ ናት "  #ዳዊት_ፀሐይ ( የፀሐፊው መብቱ የተጠበቀ ነው። ) ይች ዕለት! " 《 ሚጠተ እግዚአብሔር የሆነባት ዕለት ናት! 》 ፥ " ይቺ ዕለት! "《 እግዚአብሔር አምላክ አሕዛብን አጥፍቶ! + ትሩፋንን አውጥቶ!  ሥራውን የሰራባት ዕለት ናት! 》 ፥《 ይቺ ዕለት በነብያት ፥ ካህናት ጉባኤ ሚጠት ይሆናል ፥ ይደረጋል!  》የሚል ቃል የተሰማባት ዕለት ናት::  ፥ 《 ይቺ ዕለት እስራኤላዊያን " ከግብፅ! " የወጡባት ቀን ናት። 》 "በጉን! " ሰውተው " ከሰጠነኛው መቅሰፍት ፥ ከአስረኛው ሞተ በኩር! ፥ ከአሥራ አንደኛው ስጥመት! " የዳኑባት ዕለት ናት።   《 ይቺ ዕለት " በደብረ ሲና! " ፥ " ህግ! " የተሠራባት ዕለት ናት፡፡ " 》 《 ይቺ ዕለት  " ኖኅን! " የጠበቀው!   " አብርሃምን! " የመራው!  " ከይስሐቅ! " ጋር የተሳረ!   " ከያዕቆብ! "  ጋር እንግዳ የሆነ!  " ከዮሴፍ! " ጋር የተሸጠ!  " በሙሴ! " አድሮ ሕዝቡን የመራ! + " ሕግን! " የሰራ!  " ለኢያሱ! " እርስትን የሰጠ! + " ሕዝበ እስራኤልን! " ያወረሰ!  " በዳዊት! " አድሮ ትንቢት የተናገረ!   " በነብያት! " አድሮ ሕዝቡን ያስተማረ!  " ከእመቤታች ከቅድስት ድንግል ማርያም  የተወለደ!  《 ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስስለ እኛ ብሎ ሥጋውን የቆረሰባት ፥ ደሙን ያፈሰባት ዕለት ናት። 》 《 ይቺ ዕለት በ...

" እግዚአብሔር የሠራት ቀን ይህች ናት:- Dawit tsehay

  " እግዚአብሔር የሠራት ቀን ይህች ናት፤ ሐሤትን እናድርግ፥ በእርስዋም ደስ ይበለን።" (መዝሙረ ዳዊት 118:24፤)   " እግዚአብሔር የሠራት ቀን ይህች ናት! " ÷ " ይች ዕለት! " 《 ሚጠተ እግዚአብሔር የሆነባት ዕለት ናት! 》+ " ይቺ ዕለት! " 《 እግዚአብሔር ምላክ አሕዛብን አጥፍቶ! + ትሩፋንን አውጥቶ!  ሥራውን የሰራባት ዕለት ናት! 》 ÷《 ይቺ ዕለት በነብያት! + ካህናት! ጉባኤ ሚጠት ይሆናል! + ይደረጋል! 》 የሚል ቃል የተሰማባት ዕለት ናት::  እቺ ቀን " የመዳን! " ቀን ናት። " መድኃኒት! " የሆነባት ቀን " ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ! " ፥ " የተወደደው ሰዓት አሁን ነው፤ እነሆ፥ የመዳን ቀን ዛሬ ነው።" (2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 6:2) ሚላት " እቺ ቀን! " ናት።  " ነቢየ እግዚአብሔር ቅዱስ ኢሳይያስ! " ፥ " የሠራዊት አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል። በተወደደ ጊዜ ሰምቼሃለሁ፥ በመድኃኒትም ቀን ረድቼሃለሁ፤ እጠብቅህማለሁ፥ ምድርንም ታቀና ዘንድ፥ ውድማ የሆኑትንም ርስቶ ታወርስ ዘንድ፥ "(ትንቢተ ኢሳይያስ 49:8) የሚላት " እቺ ቀን! " ናት።  " መድሃኒትም! " አላት  እስራኤላዊያን " ከግብፅ! " የወጡባት ቀን ናት። "በጉን! " ሰውተው " ከሰጠነኛው መቅሰፍት ፥ ከአስረኛው ሞተ በኩር! " ድነውበታል፡፡  አንድም " የኤርትራን ባህር! " ተሻግረው " ከስጥመት! " የዳኑባት ቀን ናት። አንድም " በደብረ ሲና! " ፥...

የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ እና የቤተ አይሁድ ፥ የጸሐፍት ፈሪሳዊያን ፥ የካህናት አለቆች እና የህዝብ ሽማግሌዎች ጥል ምክንያት ምንድን? ነው።

  የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ እና የቤተ አይሁድ ፥ የጸሐፍት ፈሪሳዊያን ፥ የካህናት አለቆች እና የህዝብ ሽማግሌዎች ጥል ምክንያት ምንድን? ነው። ዳዊት ፀሐይ " እጅ ሊጽፈው ፥ ቃል ሊናገረው ፥ ሕሊና ሊመረምረው ከማይችው " ከገናናው ክብር። የተነሳ በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው የሚል ያ ድምፅ በመጣለት ጊዜ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ " ጌትነቱ ፦ከሙሴ ፥ ከኤልያስ በልጧል ፥ አምልኮቱ በልበ ሐዋርያት ጸንቷል ፥ በልበ ሐዋርያት " ክርስቶን ዕሩቅ ብዕሲ ፥ ወንጌልን ዲቃላ ሕግ! " ያለ ሰይጣን ድል ተነስቷል።  " አንድ ልጅም ከአባቱ ዘንድ እንዳለው ክብር የሆነው ክብሩን አየን። " (የዮሐንስ ወንጌል 1:14፤) እንዲል " አባቱ እግዚአብሔር አብ ጌትነቱን፦ በደብረ ሲና ፦ በአምሳለ እሳት እንዳሳየ ፥ እሱም ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ፦ ጌትነቱን በደብረ ታቦር ፦ በአምሳለ ብርሃን ! " ገልጧል።  አባቱ እግዚአብሔር አብ ፦ በኤልያስ አድሮ አንድ ሙት ፥ በኤልሳ አድሮ ሁለት ሙት እንዳስነሳ ፥ እሱም ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ፦ " የአራት ቀን እሬሳ አልአዛርን ፥ የእለት እሬሳ ወለተ ኢያዒሮስን ፥ ወልደ መበለትን አስነስቷል " " እርሱም የክብሩ መንጸባረቅና የባሕርዩ ምሳሌ ሆኖ፥ ሁሉን በስልጣኑ ቃል እየደገፈ! " እንዲል እርሱ ፦ " ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ " ፥ " እግዚአብሔር አብን " በመልክ የሚመስለው ፥ በባሕርይ የሚተካከለው! " ሁኖ " ብርሃነ ፀሐይ ከዓይን ጋር ተዋሕዶ ክበቡን እንዲያስታውቅ ፥ እሱም ሥጋን ተዋሕዶ   ...