የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ እና የቤተ አይሁድ ፥ የጸሐፍት ፈሪሳዊያን ፥ የካህናት አለቆች እና የህዝብ ሽማግሌዎች ጥል ምክንያት ምንድን? ነው።
የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ እና የቤተ አይሁድ ፥ የጸሐፍት ፈሪሳዊያን ፥ የካህናት አለቆች እና የህዝብ ሽማግሌዎች ጥል ምክንያት ምንድን? ነው።
ዳዊት ፀሐይ
" እጅ ሊጽፈው ፥ ቃል ሊናገረው ፥ ሕሊና ሊመረምረው ከማይችው " ከገናናው ክብር። የተነሳ በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው የሚል ያ ድምፅ በመጣለት ጊዜ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ " ጌትነቱ ፦ከሙሴ ፥ ከኤልያስ በልጧል ፥ አምልኮቱ በልበ ሐዋርያት ጸንቷል ፥ በልበ ሐዋርያት " ክርስቶን ዕሩቅ ብዕሲ ፥ ወንጌልን ዲቃላ ሕግ! " ያለ ሰይጣን ድል ተነስቷል።
" አንድ ልጅም ከአባቱ ዘንድ እንዳለው ክብር የሆነው ክብሩን አየን። " (የዮሐንስ ወንጌል 1:14፤) እንዲል " አባቱ እግዚአብሔር አብ ጌትነቱን፦ በደብረ ሲና ፦ በአምሳለ እሳት እንዳሳየ ፥ እሱም ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ፦ ጌትነቱን በደብረ ታቦር ፦ በአምሳለ ብርሃን ! " ገልጧል።
አባቱ እግዚአብሔር አብ ፦ በኤልያስ አድሮ አንድ ሙት ፥ በኤልሳ አድሮ ሁለት ሙት እንዳስነሳ ፥ እሱም ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ፦ " የአራት ቀን እሬሳ አልአዛርን ፥ የእለት እሬሳ ወለተ ኢያዒሮስን ፥ ወልደ መበለትን አስነስቷል "
" እርሱም የክብሩ መንጸባረቅና የባሕርዩ ምሳሌ ሆኖ፥ ሁሉን በስልጣኑ ቃል እየደገፈ! " እንዲል እርሱ ፦ " ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ " ፥ " እግዚአብሔር አብን " በመልክ የሚመስለው ፥ በባሕርይ የሚተካከለው! " ሁኖ " ብርሃነ ፀሐይ ከዓይን ጋር ተዋሕዶ ክበቡን እንዲያስታውቅ ፥ እሱም ሥጋን ተዋሕዶ
" እኔን ያየ አብን አየ! " ፥
" እኔ እና አብ አንድ ነን! " ፥
" ከኔ በቀር ወደ አብ የሚወጣ የለም! " እያለ አባቱን አስታውቋል፠
በዚህም ምክንያት የካህናት አለቆችና የሕዝብ ሽማግሎች በጌታችን በመደኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ቀንተዋል። ቀንተውም አልቀሩ " ወደ እርሱ ቀረቡ። በምን ሥልጣን እነዚህን ታደርጋለህ? ይህንስ ሥልጣን ማን ሰጠህ? " (የማቴዎስ ወንጌል 21:23፤) ብለዋል።
በመጽሐፍ ነብዬ እግዚአብሔር ቅዱስ ዳዊት " የተነገረውን ትንቢት ፥ የተቆጠረውን ሱባዔ! " ሳያውቁ " አሕዛብ ለምን? ያጕረመርማሉ። ወገኖችስ ለምን? ከንቱን ይናገራሉ። " (መዝሙረ ዳዊት 2:1፤) " ሕዝብም ፥ አሕዛብም! " ሲያጠፉ " ነገስታት! " ፥ " ይሰሩ ፥ ይቀጡ! " ይመስል ለምን? ወጡ። " ሕዝብም ፥ አሕዛብም ፥ ነገስታቱም! " ሲያጠፋ " ካህናት! " ፥ " ይመክሩ ፥ ያስተምሩ! " ይመስል ለምን? ወጡ። " በእግዚአብሔር! " ላይ በጠላትነት ለመነሳት እንጂ! " እንዲል የካህናት አለቆች እና የህዝብ ሽማግሌዎች በጠላትነት ተነሱ።
ነገር ግን፦ በሰማይ የሚኖር እርሱ ይሥቃል፥ ጌታም ይሣለቅባቸዋል።" (መዝሙረ ዳዊት 2:4፤) " መልአኩ ይስቃል ፥ እግዚአብሔርም ይሳለቃል " ሲል " ነቢየ እግዚአብሔር ቅዱስ ዳዊት! " ፥ " በመልአኩ! " ሳቅ ፥ " በእግዚአብሔርም! " ስላቅ ኑሮ አይደለም እንደ " ሚፈርድባቸው! " ሲናገር ነው። ተብሎ እንደ ተጻፈ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሊፈርድባቸው እንዲህ አለ።
" የወይን አትክልት የተከለ ባለቤት ሰው ነበረ፤ ቅጥርም ቀጠረለት፥ መጥመቂያም ማሰለት፥ ግንብም ሠራና ለገበሬዎች አከራይቶ ወደ ሌላ አገር ሄደ።" የሚያፈራበትም ጊዜ ሲቀርብ፥ ፍሬውን ሊቀበሉ ባሮቹን ወደ ገበሬዎች ላከ። ገበሬዎቹም ባሮቹን ይዘው አንዱን ደበደቡት አንዱንም ገደሉት ሌላውንም ወገሩት። ደግሞ ከፊተኞች የሚበዙ ሌሎች ባሮችን ላከ፥ እንዲሁም አደረጉባቸው። በኋላ ግን። ልጄንስ ያፍሩታል ብሎ ልጁን ላከባቸው።ገበሬዎቹ ግን ልጁን ባዩ ጊዜ እርስ በርሳቸው። ወራሹ ይህ ነው፤ ኑ፥ እንግደለውና ርስቱን እናግኝ ተባባሉ። ይዘውም ከወይኑ አትክልት አወጡና ገደሉት።
እንግዲህ የወይኑ አትክልት ጌታ በሚመጣ ጊዜ በእነዚህ ገበሬዎች ምን ያደርግባቸዋል? እነርሱም። ክፉዎችን በክፉ ያጠፋቸዋል፥ የወይኑንም አትክልት ፍሬውን በየጊዜው ለሚያስረክቡ ለሌሎች ገበሬዎች ይሰጠዋል አሉት። እንዲህም ብለው አልቀሩ " የካህናት አለቆችና ፈሪሳውያንም ምሳሌዎቹን ሰምተው ስለ እነርሱ እንደ ተናገረ አስተዋሉ፤" (የማቴዎስ ወንጌል 21:45፤) በዚህ ጊዜ " ፈራጅነቱን! " አውቀው (የሉቃስ ወንጌል 20:16፤) ፥ " ጌታ ሆይ ይህስ አይሁን! " ፥ " አትፍረድ! " አሉት። " ጌታችን መድኃታችን ኢየሱስ ክርስቶስ! " ፥ " ፈራጅ! " ነው።
ቤተ አይሁድ ፥ ጸሐፍት ፈሪሳዊያን ፥ የካህናት አለቆች እና የህዝብ ሽማግሌዎች ከጌታችን ከመድኃኒታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር የተጣሉት አምላክነቱን ሳያውቁ ፥ ሳይረዱ ቀርተው አይደለም።
ኦሪት እንዳታልፍባቸው ፥
ክህነታቸው እንዳይሻርባቸው ፥
መሥዋዕታቸው ፦ ደመ ላሕም ፥ ደመ በግ ፥ ደመ ጠሊ! " እንዳይቀርባቸው ፈርተው ነው።
በዛውም ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ " ግንበኞች የናቁት ድንጋይ እርሱ የማዕዘን ራስ ሆነ፤ ይህም ከጌታ ዘንድ ሆነ፥ ለዓይኖቻችንም ድንቅ ነው የሚለውን ከቶ በመጽሐፍ አላነበባችሁምን? ፥ በዚህም ድንጋይ ላይ የሚወድቅ ይቀጠቀጣል፤ ድንጋዩ ግን የሚወድቅበትን ሁሉ ይፈጨዋል።" (የማቴዎስ ወንጌል 21:42፤) ብሎ " ግንበኞች የናቁት ድንጋይ! " እርሱ መሆኑን ነግሯቸዋል።
በቀጣይ ምዕራፍ

Comments
Post a Comment