#ዳዊት_ፀሐይ #እንኳን_አደረሳችሁ " ነቢዬ እግዚአብሔር ቅዱስ ዳንኤል! "፦ " ዙፋኖችም እስኪዘረጉ ድረስ አየሁ ፥ በዘመናት የሸመገለውም ተቀመጠ። ይለዋል " እግዚአብሔር አብን! " ነው። ይህን ጉዳይ " ቅዱስ ጎርጎርዮስ! ፦ " አምላክነ ዘእንበለ ጥንት ፥ ወመድኃኒነ ዘእንበለ ተፍጻሜት! " ፥ " ጥንት የሌለው አምላክ ፥ ፍጻሜ የሌለው መድኃኒት! " እያለ ይጠቅሰዋል። " እሱ ፥ እራሱ፦ " እግዚአብሔር አብ " <<ያለና የሚኖር>> እኔ ነኝ! " (ኦሪት ዘጸአት 3:14፤) እንዲል " ሕልፈት ፥ ውላጤ! " የማይስማማው ፥ " ጉም ፥ ደመና! " የማይጋርደው ፥ " እሳት ፥ ባሕር! " የማይከለክለው ፥ " በዚህ አለ ፥ በዚህ የለም! " የማይባል ፥ " ለዘመኑ ሕልፈት ፥ ለግዛቱ ወሰን! " የሌለው አምላክ ነው። እና ለዘመኑ " ጥንት! " ተብሎ ስለ ማይነገርለት " ነቢዬ እግዚአብሔር ቅዱስ ዳንኤል! " ፥ " በዘመናት የሸመገለው! " አለው። ምንም እንኳ ፍጥረት የፈጠረ እርሱ ቢሆንም እርሱ፦ ብርሃናት ሳይመላለሱ ፥ ነፋሳት ሳይነፍሱ ፥ ማያት ( ወንዞች ) ሳይፈሱ ፥ ቀን እና ሌሊት ፥ ክረምት እና በጋ ሳይፈራረቁ እሱ ነበረ። ይሄን ሲያይ " በዘመናት የሸመገለው! " አለው። እንደ ገናም ነቢዩ " ልብሱም እንደ በረዶ ነጭ፥ የራሱም ጠጕር እንደ ጥሩ ጥጥ ነበረ፤ ዙፋኑም የእሳት ነበልባል ነበረ፥ መንኰራኵሮቹም የሚነድድ እሳት ነበሩ። "(ትንቢተ ዳንኤል 7:9፤) ይለዋል። ቅዱስ ቄ...
የመስቀሉ ነገር..... #ዳዊት_ፀሐይ ( የፀሐፊው መብቱ የተጠበቀ ነው። ) 《 ዐይን ያላየው ፥ ጀሮ ያልሰማው ፥ በሰው ልቡና ያልታሰበ ፥ " እኛ ልንከብርበት እግዚአብሔር ያከናወነው ፥ ዓለም ሳይፈጠር ያነጸው ፥ ያጸናው《 ነገረ መስቀል! 》ነው:: (1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 2: 7-10 ) " የምናገረው ነገር! + የማስተምረው ትምርት! " የሰውነት ልባምነት በማታለል አይደለም:: መንፈስ ቅዱስ ባደረብኝ " ቋንቋ! " በመናገር! + መንፈስ ቅዱስ በገለጠው " ምሥጢር! " በመግለጥ ነው:: 《 ድዊ በመፈወስ! + ለምጻም በማንጻት! + ጋኔን በማውጣት! + ሙት በማስነሳት! 》ነው:: " ጠቢባን! " ነን ለሚሉ ሰዎች " ጥበብን! " እነግራቸዋለሁ:: የምነግራቸው " ጥበብ! " የዚህ ዓለም ነገስታት! + የዚህ ዓለም ፈላስፎች! የሚያዉቁትን " ጥበብ! " አይደለም:: የዚህ ዓለም ነገስታት! + የዚህ ዓለም ፈላስፎች! የላወቁትን 《 ከእግዚአብሔር የተገኘውን እውነተኛ ጥበብን ነው:: 》 ይህን《 " ጥበብ! " አውቀውትስ ቢሆን ኑሮ! + የክብርን ጌታ! + ባልሰቀሉት ነበር!》 ስለዚህም ነገር " ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ! " 《 አባት ሆይ፥ የሰማይና የምድር ጌታ፥ ይህን " ጥበብ! " ከጥበበኞች! እና ከአስተዋዮች! + ጠበበኛ! እና አስተዋይ! " ነን! " ከሚሉት " ከጻሕፍተ ሰፈርሳዊ...