Skip to main content

" ዕለተ ዐርብ፦ እግዚአብሔር የሠራት ቀን ይቺ ናት " Dawit tsehay


 " ዕለተ ዐርብ፦ እግዚአብሔር የሠራት ቀን ይቺ ናት " 


#ዳዊት_ፀሐይ ( የፀሐፊው መብቱ የተጠበቀ ነው። )


ይች ዕለት! " 《 ሚጠተ እግዚአብሔር የሆነባት ዕለት ናት! 》


፥ " ይቺ ዕለት! "《 እግዚአብሔር አምላክ አሕዛብን አጥፍቶ! + ትሩፋንን አውጥቶ!  ሥራውን የሰራባት ዕለት ናት! 》


፥《 ይቺ ዕለት በነብያት ፥ ካህናት ጉባኤ ሚጠት ይሆናል ፥ ይደረጋል!  》የሚል ቃል የተሰማባት ዕለት ናት:: 


፥ 《 ይቺ ዕለት እስራኤላዊያን " ከግብፅ! " የወጡባት ቀን ናት። 》


"በጉን! " ሰውተው " ከሰጠነኛው መቅሰፍት ፥ ከአስረኛው ሞተ በኩር! ፥ ከአሥራ አንደኛው ስጥመት! " የዳኑባት ዕለት ናት። 


 《 ይቺ ዕለት " በደብረ ሲና! " ፥ " ህግ! " የተሠራባት ዕለት ናት፡፡ " 》


《 ይቺ ዕለት  " ኖኅን! " የጠበቀው! 

 " አብርሃምን! " የመራው!

 " ከይስሐቅ! " ጋር የተሳረ! 

 " ከያዕቆብ! "  ጋር እንግዳ የሆነ!

 " ከዮሴፍ! " ጋር የተሸጠ!

 " በሙሴ! " አድሮ ሕዝቡን የመራ! + " ሕግን! " የሰራ!

 " ለኢያሱ! " እርስትን የሰጠ! + " ሕዝበ እስራኤልን! " ያወረሰ!

 " በዳዊት! " አድሮ ትንቢት የተናገረ! 

 " በነብያት! " አድሮ ሕዝቡን ያስተማረ!

 " ከእመቤታች ከቅድስት ድንግል ማርያም  የተወለደ! 


《 ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስስለ እኛ ብሎ ሥጋውን የቆረሰባት ፥ ደሙን ያፈሰባት ዕለት ናት። 》


《 ይቺ ዕለት በነብይ  " እግዚአብሔር አለኝ " አንተ ልጄ ነህ፥ እኔ ዛሬ ወለድሁህ።"

(መዝሙረ ዳዊት 2:7፤) የተባለው የተፈጸመባት ዕለት ናት። 》


" አንተ ልጄ ነህ! " አለ አካል ዘእም አካል ፥  ባሕርይ ዘእም ባሕርይ ወለድኩህ ሲለው ነው። " እኔ ዛሬ ወለድሁህ።" ሲለው ግን ሁለተኛ የሚወልደው ሁኖ አይደለም። ስለ ሥራው " ሥጋውን ቆርሶ ፥ ደሙን አፍሶ ፥  ሲኦል ወርዶ! " ነፍሳትን ማውጣቱን ሲናገር ነው። 


አንድ " አርበኛ! " አለ። ዘምቶ አርጅቷል ፥ ፈጅቶ አፋጅቷል። ህዝቡን ሰብስቦ ፥ ልጁን አስጠርቶ " ልጄ! " ይለዋል። " ዘምቼ አረጀው ፥ ፈጅቼ አፋጀው ፥ አንተ ልጄ ነህ ፥ በርስቴ ውጣበት ፥ በጉልቴ ውረድበት! " ይለዋል። ልጁም " ወጣሁ ልጅ ነኝ ፥ ፈላሁ ጠጅ ነኝ! " ብሎ ፥ " እግሩን ለጠጠር ፥ ደረቱን ለጦር! " ሰጦ ይዘምታል። ሲመለስ " አባቴ! " ፥ " በርስቴ ውጣበት ፥ በጉልቴ ውረድበት! " ብለህ በሰጠኽኝ ቦታ " ከርስት ላይ ርስት ፥ ከጉልት ላይ ጉልት! " ጨምሬበት መጣሁ! " ይለዋል። አባቱም " ቀድሞ ልጄ ነበርክ ፥ ልጅ መሆንክን አስመሰከርክ ፥ እኔ ዛሬ ወለድኩህ! "


እንደ ሚለው ሁሉ " ጌታም ፥ ጌታችን መድኅኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ! " ከአቤል ጀምሮ እስከ ዕለተ አርብ ያሉትን ነፍሳት " ሥጋውን ቆርሶ ፥ ደሙን አፍሶ ፥ በአካለ ነፍስ ሲኦል ወርዶ! " ፥


" እለ ውስተ ሲኦል ፃዑ፦ በሲኦል ያላችሁ ውጡ! " 


" ወእለ ውስተ ጽልመት ተከስቱ፦ በጨለማ ያላችሁ ተገለጡ! " 


" ወርእዩ ብርሃን ዐቢየ፦ ኑ ብርሃኑን እዩት! " 

ብሎ በጠራቸው ጊዜ ፥ በገነት አድርጎ ባረገ ጊዜ ፥ " እኔ ዛሬ ወለድኩህ! " አለው " አባቱ  እግዚአብሔር አብ። "

Comments