" በመገረፉ ቁስል ተፈወሳችሁ። እንደ በጎች ትቅበዘበዙ ነበርና፥ አሁን ግን ወደ ነፍሳችሁ እረኛና ጠባቂ ተመልሳችኋል። "
(1ኛ የጴጥሮስ መልእክት 2:25፤)
#ዳዊት_ፀሐይ ( የፀሐፊው መብቱ የተጠበቀ ነው። )
" እንደ በጎች ትቅበዘበዙ ነበር! " አለ 《 እንደ ታመመ በግ! 》 ማለት ነው:: የተመመን በግ ከመጋው ለይተው! + ከደረቅ ቦታ አስረው! + ደረቅ ሣር! + ጥሩ ውኃ ይመግቡታል! + ሲድን ታቅፈው ቀስደው ከመንጋው ይጨምሩታል:: " እንደ ታመመ በግ! " አለ 《 " ታሞ! " የነበረ ገነትን ያህል ቦታ! + እግዚአብሔርን ያህል ጌታ! አጦ የነበረ " አዳም! " ነው:: " 》" ከመንጋው እንደ መለየት! " 《 አዳምም ከማኅበረ መላእክት ተለይቷል! 》" ከደረቅ ቦታ አስረው! + ደረቅ ሣር! + ጥሩ ውኃ! እንዲመግቡት! " 《 ነፍሶሙሰ ለጻድቃን ውስተ እደ እግዚአብሔር ወኢለከፎሙ ላህበ ሥቃይ ወኢምንትኒ! 》 እንዲል《 5500 ዘመን በእደ እግዚአብሔር ሲጠበቅ ኑሯል! 》" ሲድን ወስደው ከመንጋው እንዲጨምሩት! " 《 ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስም ባሕርዩን በሕርይ አድርጎ! + ጽንዓ ነፍስን ሰጥቶ አድኖታል! 》
" ክብር ምሥጋና ለአግዚአብሔር ይሁን። "

Comments
Post a Comment