Skip to main content

" እግዚአብሔር የሠራት ቀን ይህች ናት:- Dawit tsehay

 

" እግዚአብሔር የሠራት ቀን ይህች ናት፤ ሐሤትን እናድርግ፥ በእርስዋም ደስ ይበለን።"

(መዝሙረ ዳዊት 118:24፤) 

 " እግዚአብሔር የሠራት ቀን ይህች ናት! " ÷ " ይች ዕለት! " 《 ሚጠተ እግዚአብሔር የሆነባት ዕለት ናት! 》+ " ይቺ ዕለት! " 《 እግዚአብሔር ምላክ አሕዛብን አጥፍቶ! + ትሩፋንን አውጥቶ!  ሥራውን የሰራባት ዕለት ናት! 》 ÷《 ይቺ ዕለት በነብያት! + ካህናት! ጉባኤ ሚጠት ይሆናል! + ይደረጋል! 》 የሚል ቃል የተሰማባት ዕለት ናት:: 

እቺ ቀን " የመዳን! " ቀን ናት። " መድኃኒት! " የሆነባት ቀን " ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ! " ፥ " የተወደደው ሰዓት አሁን ነው፤ እነሆ፥ የመዳን ቀን ዛሬ ነው።" (2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 6:2) ሚላት " እቺ ቀን! " ናት። 

" ነቢየ እግዚአብሔር ቅዱስ ኢሳይያስ! " ፥ " የሠራዊት አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል። በተወደደ ጊዜ ሰምቼሃለሁ፥ በመድኃኒትም ቀን ረድቼሃለሁ፤ እጠብቅህማለሁ፥ ምድርንም ታቀና ዘንድ፥ ውድማ የሆኑትንም ርስቶ ታወርስ ዘንድ፥ "(ትንቢተ ኢሳይያስ 49:8) የሚላት " እቺ ቀን! " ናት። 

" መድሃኒትም! " አላት 

እስራኤላዊያን " ከግብፅ! " የወጡባት ቀን ናት።

"በጉን! " ሰውተው " ከሰጠነኛው መቅሰፍት ፥ ከአስረኛው ሞተ በኩር! " ድነውበታል፡፡ 

አንድም " የኤርትራን ባህር! " ተሻግረው " ከስጥመት! " የዳኑባት ቀን ናት።

አንድም " በደብረ ሲና! " ፥ " ህግ! " የተሰራባት ቀን ናት፡፡ " መድሃኒትም! " አላት

" ከአምልኮተ ጣኦት! " ድነውበታል፡፡ 

አንድም ያች ቀን " መጋቢት 27! " የዛሬይቱ " ቀን! " ናት። 

አንድም ይቺ ዕለተ ኖኅን! " የጠበቀው! 

 " አብርሃምን! " የመራው 

 " ከይስሐቅ! " ጋር የተሳረ! 

 " ከያዕቆብ! "  ጋር እንግዳ የሆነ!

 " ከዮሴፍ! " ጋር የተሸጠ!

 " በሙሴ! " አድሮ ሕዝቡን የመራ! + " ሕግን! " የሰራ!

 " ለኢያሱ! " እርስትን የሰጠ! + " ሕዝበ እስራኤልን! " ያወረሰ!

 " በዳዊት! " አድሮ ትንቢት የተናገረ! 

 " በነብያት! " አድሮ ሕዝቡን ያስተማረ!

 " ከእመቤታች ከቅድስት ድንግል ማርያም! " የተወለደ! 

《 ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ! 》 ነው።

" ኢየሱስ ክርስቶስን! " ደግሞ

 《 በመልክ የሚመስለው ፥ በባሕርይ የሚተካከለው! 》 የለም።

 እርሱ " እግዚአብሔር! " የሆነ እንደ 《 ዲያቢሎስ ተመቃኝቶ ፥ እንደ አዳም ተመኝቶ! 》አይደለም። እስከ ሞት ድረስ " ለመስቀል ሞት እንኳ የታዘዘ ሆነ።"

(ወደ ፊልጵስዩስ ሰዎች 2:8፤) እንደ ተባለ ታዛዥ ሁኖ ነው። በዚህም ምክንያት የከበረ ስምን ሰጠው " ይህም በሰማይና በምድር ከምድርም በታች ያሉት ሁሉ በኢየሱስ ስም ይንበረከኩ ዘንድ፥"

(ወደ ፊልጵስዩስ ሰዎች 2:10፤) 


" እግዚአብሔር አለኝ " አንተ ልጄ ነህ፥ እኔ ዛሬ ወለድሁህ።"

(መዝሙረ ዳዊት 2:7፤) የተባለበት ቀን ናት።


አንተ ልጄ ነህ አለ አካል ዘእም አካል ባሕርይ ዘእም ባሕርይ ወለድኩህ ሲለው ነው። እኔ ዛሬ ወለድሁህ።" ሲለው ግን ሁለተኛ የሚወልደው ሁኖ አይደለም ስለ ስራው ሥጋውን ቆርሶ ደሙን አፍሶ ሲኦል ወርዶ ነፍሳትን ማውጣቱን ሲናገር ነው። 


አንድ አርበኛ አለ ዘምቶ አርጅቷል ፈጅቶ አፋጅቷል። ህዝቡን ሰብስቦ ልጁን አስጠርቶ ልጄ ይለዋል ዘምቼ አረጀው ፈጅቼ አፋጀው አንተ ልጄ ነህ በርስቴ ውጣበት በጉልቴ ውረድበት ይለዋል። ልጁም ወጣሁ ልጅ ነኝ ፈላሁ ጠጅ ነኝ ብሎ እግሩን ለጠጠር ደረቱን ለጦር ሰጦ ይዘምታል። ሲመለስ አባቴ በርስቴ ውጣበት በጉልቴ ውረድበት ብለህ በሰጠኽኝ ቦታ ከርስት ላይ ርስት ከጉልት ላይ ጉልት ጨምሬበት መጣሁ ይለዋል። አባቱም ቀድሞ ልጄ ነበርክ ልጅ መሆንክን አስመሰከርክ እኔ ዛሬ ወለድኩህ


 እንደ ሚለው ሁሉ ጌታም ጌታችን መድኅኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከአቤል ጀምሮ እስከ ዕለተ አርብ ያሉትን ነፍሳት ሥጋውን ቆርሶ ደሙን አፍሶ በአካለ ነፍስ ሲኦል ወርዶ 

እለ ውስተ ሲኦል ፃዑ

ወእለ ውስተ ጽልመት ተከስቱ 

ወርእዩ ብርሃን ዐቢየ ብሎ በገነት አድርጎ ባረገ ጊዜ እኔ ዛሬ ወለድኩህ አለው እግዚአብሔር አብ።


2🙋 አንድም እቺ ዕለት " ደስታ ፥ ሰላም ፥ ምሕረት! " የተፈፀመባት ዕለት ናት። 


የተስፍ ባለቤት! + የምሕረት መገኛ! " እግዚአብሔር ነው ፠ " ልጅ! " ከአባት እንዲገኝ! + ተስፋ እና ምሕረት አስገኛቸው እሱ ነው ፠  ለዚህም ነው " አቡሃ ለምሕረት ወለ ተስፋ! " የሚለው ፠ " እንዲህ ከሆነም የተስፋው ባለቤት ተስፋውን! + የደስታው ባለቤት ደስታውን! + የሰላም ባለቤት ሰላሙን! ይፈጽምላችሁ ፠ " እቺም ተስፍ! + እቺም ደስታ! + እቺም ሰላም!  " መንግሰተ ሰማያት! " + አንድም " ወንጌል ናት! " ፠ እቺ " ወንጌል! " ወልደ እግዚአብሔር ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንደ ነገሰ! + ዲያቢሎስ እንደ ተሻረ! + ሞተ ስጋ! + ሞተ ነፍስ! እንደ ጠፋ!  ያወቅንበት ነው፠


3🙋 " የመስቀሉ ቃል ለሚጠፉት ሞኝነት፥ ለእኛ ለምንድን ግን የእግዚአብሔር ኃይል ነውና።"

(1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 1:18፤) እንዳለ በዚች ቀን " እናቱን እናታችን " ቅድስት ድንግል ማርያምን! " ሰጦናል። ስለዚህም ነገር " አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ! " 


《 እግዚአብሔር " ያዝነው ፥ አንለቀውም! " 

     እርሱም " አቀፈን ፥ አልተወንም! " 

     በመስቀሉ ወደ " እናቱ! " አቀረበን!


     ከእሷ ወደ የትም? እንዳንሸሽ!


     እንደ " ቀለበት! " በጣታችን! ፥ 

     እንደ " ማኅተም! " በክንዳችን 

     ከመቀነቷ ጋር አሰረን! " 》


     " እግዚአብሔር ፥ ይመስገን! " 


     እሷም " ሐር! " ናት ለብሰናታል! 

     እሷም " ሰይፍ! " ናት ታጥቀናታል!

     እሷም " ጋሿ! " ናት ተደግፈናታል። ይላል።


" ያደነንም ፥ በቅዱሱም አጠራር የጠራን ጌታ እግዚአብሔር ነው! " (2ኛ ወደ ጢሞቴዎስ 1:9፤) እንዲል 

ያዳነንም " በደሙ! " ነው። 


" ደሙ! " ደግሞ 


" ሲሩያነ በምሕረትከ አንፅሕ! " 


" የኢየሱስ ክርስቶስ ደም ከኃጢአት ሁሉ ያነጻናል።"

(1ኛ የዮሐንስ መልእክት 1:7፤ ) እንደ ተባለ


" ልብስ በደም ፥

  ፀምር ፥ ግምጃ ፥ በቀለም

  እንዲታለል ፥ እንዲነከር! " ፥ 


ይህ " ደም! "   


" በኃጢአት የታለሉትን በቸርነቱ ያነጻል! "  


አንድም 


  " በኃጢአት የሄዱትን ፥ በመግባር የተናወጹት! " 

  "  ምግባር ፥ትሩፋት ፥ ከመስራት! " የተቆጠቡትን

  " በደሙ ፈዋሽነት ያነጻል። "

     አንጽቶናልም።


ስለዚህም ነገር " ነቢየ እግዚአብሔር ቅዱስ ዳዊት! " ፥ 

" ወድዶኛልና አዳነኝ።"

(መዝሙረ ዳዊት 18:19፤) ይላል።


 ሲወደኝም ከነ " ኅጥያቴ! " ፥ ከነ " በደሌ! " 


" በእጄ መግደል ፥

  በቃሌ መበደል ፥

  በልቦናዬ ቂም በቀል! "  ይዤ ነው።


 እኔን ከመውደዱ የተነሳ ግን


" ደመናት ዝናብ እያዘነቡ ሄዱ! " 


 " ጸልሙ ማያት በውስተ ደመናት! " ( ውኖች በደመና ጠቆሩ!  ) እንዲል!

 《  የዝናብ! 》አመጣጥ እንዲህ ነው:: 

" የውኃ! እና የደመና! ኅብራቸው ( ቀለማቸው! ) " ነጭ! " ነው::

《 የውቂያኖስ ውኃ! +

    በደመና አይበት ተነስቶ! + 

    በነፋስ  ወደል ጋዝ  ተጭኖ ! + 

    ከውቂያኖስ ሲወጣ ሲታይ " ጠቁሮ! " ይታያል!  ፥

  ከዛ " ( ወገዘፈ


ደመናት በራእየ ነፋሳት! ) ይላል

  " ደመናው " በነፋስ! "  አማካኝነት ይገዝፋል! + ያድጋል! + ይመነደጋል! 

   ከዛ ከሰበበት ቦታ ሲደርስ ይዘንባል:: ይላል። 


  ይህ ደግሞ " የመዳኔ ምልክት! " ነው። 


ያዳነንም " ጌታችን መድኃኒታችን " ኢየሱስ ክርስቶስ! " መድኅን ዓለም " መድኃኔዓለም! " ነው።

እሱ ደግሞ


  ዘንድ ነው። " ኢየሱስ ክርስቶስ ፥ የእግዚአብሔር ልጅ! " ተባለ።


በእርሱ " ቁስል! " ደግሞ እኛ ተፈወሰን። 


" በመገረፉ ቁስል ተፈወሳችሁ። እንደ በጎች ትቅበዘበዙ ነበርና፥ አሁን ግን ወደ ነፍሳችሁ እረኛና ጠባቂ ተመልሳችኋል።"

(1ኛ የጴጥሮስ መልእክት 2:25፤)


" እንደ በጎች ትቅበዘበዙ ነበር! " አለ 《 እንደ ታመመ በግ! 》 ማለት ነው:: የተመመን በግ ከመጋው ለይተው! +  ከደረቅ ቦታ አስረው! +  ደረቅ ሣር! + ጥሩ ውኃ ይመግቡታል! + ሲድን ታቅፈው ቀስደው ከመንጋው ይጨምሩታል:: " እንደ ታመመ በግ! "  አለ 《 " ታሞ! "  የነበረ ገነትን ያህል ቦታ! +  እግዚአብሔርን ያህል ጌታ!  አጦ የነበረ " አዳም! " ነው:: " 》" ከመንጋው እንደ መለየት! " 《 አዳምም ከማኅበረ መላእክት ተለይቷል! 》"  ከደረቅ ቦታ አስረው! + ደረቅ ሣር! + ጥሩ ውኃ!  እንዲመግቡት! " 《  ነፍሶሙሰ ለጻድቃን ውስተ እደ እግዚአብሔር ወኢለከፎሙ ላህበ ሥቃይ ወኢምንትኒ! 》 እንዲል《 5500 ዘመን በእደ እግዚአብሔር ሲጠበቅ ኑሯል! 》" ሲድን ወስደው ከመንጋው እንዲጨምሩት! " 《 ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስም ባሕርዩን በሕርይ አድርጎ! + ጽንዓ ነፍስን ሰጥቶ አድኖታል! 》 


"24፤ እግዚአብሔር የሠራት ቀን ይህች ናት፤ ሐሤትን እናድርግ፥ በእርስዋም ደስ ይበለን።"

(መዝሙረ ዳዊት 118:24፤)


 "10፤ ከአእላፍ ይልቅ በአደባባዮችህ አንዲት ቀን ትሻላለች፤ በኃጥኣን ድንኳኖች ከመቀመጥ ይልቅ፥ በእግዚአብሔር ቤት እጣል ዘንድ መረጥሁ።"

(መዝሙረ ዳዊት 84:10፤)


"13፤ ፈቃድህን በተቀደሰው ቀኔ ከማድረግ እግርህን ከሰንበት ብትመልስ፥ ሰንበትንም ደስታ፥ እግዚአብሔርም የቀደሰውን ክቡር ብትለው፥ የገዛ መንገድህንም ከማድረግ ፈቃድህንም ከማግኘት ከንቱ ነገርንም ከመናገር ተከልክለህ ብታከብረው፥"

(ትንቢተ ኢሳይያስ 58:13፤)


"10፤ እርሱም። ሂዱ፥ የሰባውንም ብሉ፥ ጣፋጩንም ጠጡ፥ ለእነዚያም ላልተዘጋጀላቸው እድል ፈንታቸውን ስደዱ፤ ዛሬ ለጌታችን የተቀደሰ ቀን ነው፤ የእግዚአብሔርም ደስታ ኃይላችሁ ነውና አትዘኑ አላቸው። "

(መጽሐፈ ነሀምያ 8:10፤)


"10፤ በጌታ ቀን በመንፈስ ነበርሁ፥ በኋላዬም የመለከትን ድምፅ የሚመስል ትላቅ ድምፅ ሰማሁ፥"

(የዮሐንስ ራእይ 1:10፤)


"9፤ በኢያሱ ፊት ያኖርሁት ድንጋይ እነሆ አለ፤ በአንዱ ድንጋይ ላይ ሰባት ዓይኖች አሉ፤ እነሆ፥ ቅርጹን እቀርጻለሁ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፥ የዚያችንም ምድር በደል በአንድ ቀን አስወግዳለሁ። "

(ትንቢተ ዘካርያስ 3:9፤)

Comments