የመስቀሉ ነገር.....
#ዳዊት_ፀሐይ ( የፀሐፊው መብቱ የተጠበቀ ነው። )
《 ዐይን ያላየው ፥
ጀሮ ያልሰማው ፥
በሰው ልቡና ያልታሰበ ፥
" እኛ ልንከብርበት እግዚአብሔር ያከናወነው ፥ ዓለም ሳይፈጠር ያነጸው ፥ ያጸናው《 ነገረ መስቀል! 》ነው::
(1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 2: 7-10 )
" የምናገረው ነገር! + የማስተምረው ትምርት! " የሰውነት ልባምነት በማታለል አይደለም:: መንፈስ ቅዱስ ባደረብኝ " ቋንቋ! " በመናገር! + መንፈስ ቅዱስ በገለጠው " ምሥጢር! " በመግለጥ ነው::
《 ድዊ በመፈወስ! +
ለምጻም በማንጻት! +
ጋኔን በማውጣት! +
ሙት በማስነሳት! 》ነው::
" ጠቢባን! " ነን ለሚሉ ሰዎች " ጥበብን! " እነግራቸዋለሁ:: የምነግራቸው " ጥበብ! " የዚህ ዓለም ነገስታት! + የዚህ ዓለም ፈላስፎች! የሚያዉቁትን " ጥበብ! " አይደለም:: የዚህ ዓለም ነገስታት! + የዚህ ዓለም ፈላስፎች! የላወቁትን
《 ከእግዚአብሔር የተገኘውን እውነተኛ ጥበብን ነው:: 》
ይህን《 " ጥበብ! " አውቀውትስ ቢሆን ኑሮ! + የክብርን ጌታ! + ባልሰቀሉት ነበር!》
ስለዚህም ነገር " ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ! "
《 አባት ሆይ፥ የሰማይና የምድር ጌታ፥ ይህን " ጥበብ! " ከጥበበኞች! እና ከአስተዋዮች! + ጠበበኛ! እና አስተዋይ! " ነን! " ከሚሉት " ከጻሕፍተ ሰፈርሳዊያን! " ሰውረህ! + ለሕፃናት " ለሐዋርያት! " ስለ ገለጥህላቸው አመሰግንሃለሁ፤"
(የማቴዎስ ወንጌል 11:25፤) እንዳለ " ጌታ እግዚአብሔር! " ጠበበኛ! እና አስተዋይ! " ነን! " ከሚሉት ይልቅ " አልተማርነም! + አናስተውልም! " ለሚሉት ጥበብን! + ምሥጢርን! መግለጥ ልማዱ ነው::
አስቀድሞ 《 ነገረ ድኅነት! 》 የተገለጠ " ጠበበኛ! እና አስተዋይ! " " ነን! " ለሚሉት 《 ለሰባ ትካት! እና ለሰባ ሰዶም! 》ሳይሆን " አልተማርነም! + አናስተውልም! " ለሚሉት 《 ለኖኅ! እና ለሎጥ! 》ነው::
ስለዚህም ነገር 》ስለ《 ነገረ መስቀል! 》ቅዱስ " እልመስጦግያ! "
ይሄ " ጥበብ! 《 ከእግዚአብሔር የማይርቅ! +
መቸም የማይለይ! +
በምንም! + በምንም የማትመጠን! +
የእግዚአብሔርን " ቸርነቱ! " + የተገለጠበት! + እረቂቅ ምሥጢር ነው:: 》አለ::
ሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስም ስለ《 ነገረ መስቀል! 》
《 ለኃጢአት ሞተን ለጽድቅ እንድንኖር፥ እርሱ ራሱ በሥጋው ኃጢአታችንን በእንጨት ላይ ተሸከመ፤ 》
(1ኛ የጴጥሮስ መልእክት 2:24፤ ) አለ::
" በዕንጨት መሰቀሉ ስለ ምን? ነው:: " ያልን እንደ ሆነ! 《 እሾህ! + በሾህ! ይነቀሳል! + ነገር በነገር ይወቀሳል! 》እንዲሉ! " በዕፅ! " ምክንያት የገባውን ሞት! + " በዕፅ! " ምክንያት ለማውጣት ነው:: " መሰቀሉ! ለምን? " ካልነም
《 ትንቢቱ! + ምሳሌው! 》 ይፈፀም ዘንድ ነው::
" እግዚአብሔር አምላክ እስራኤላዊያንን《 " መና! " ከደመና አውርዶ! + " ውኃ! " ከድንጋይ አፍልቆ! 》ቢመግባቸው! + ከዚህ 《 " ሰማዩ! " ዝቅ! + " ምድሩ! " ብቅ! 》 ካለበት ቦታ 《 " ውርጩን! " እያረጋ " መና! " ከደመና አወረድኩላችሁ! 》 ይላል እንጂ! 《 " ቆላ! " ቢሆን አይቻለውም! 》 ብለዋል::
እግዚአብሔር አምላክም " ሙሴን! " ጠርቶ《 ቆላተ ሐራሴቦን! 》ይባላል " ይዘኃቸው ውረድ! " ብሎታል:: ይዟቸው ወረደ《 " ምግቡ! + መናው! " 》 አልቀረባቸውም:: ነገር ግን 《 ነዘር እባብ! 》ይባላል እሱ ተነስቶ የሚፈጃቸው ሁኗል:: ከሙሴ ዘንድ ሂደው《 " ከኛ ኃጢአት! + ጥፋት! " + " ከእግዚአብሔር ምሕረት! + ቸርነት! አይታጣም! " 》እና " ወደ እግዚአብሔር አመልክትልን! " አሉት:: ሙሴም ቢያመለክትላቸው "《 የነሐስ እባባ! 》ሰርተህ በሚገናኙበት አደባባይ ስቀልላቸው! +《 የጸናበት ድምፁን ሰምቶ! + ያልጸናበት መልኩን አይቶ! 》 ይድናል! " ብሎታል::
ይህም " ምሳሌ! " ነው:: " ነዝር እባብ! 《 የዲያቢሎስ! 》+ ነዝር እባብ! " መርዝ! " እንዳለበት ሁሉ ከዲያቢሎስም! " ፍዳ! + መርገም! " አለበት:: "
" የነሐሱ እባብ! "《 የጌታ የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ! 》የነሐሱ እባብ! " መርዝ! " እንደ ሌሌበት ሁሉ በጌታም " ኃጢአት! + መርገም! " የለበትም! + አልተገኘበትም! :: " መልኩን አይተው የዳኑ! " 《 በጌታ ስብከት ያመኑ! 》 + " ድምፁን ሰምተው የዳኑ! " 《 ከጌታ በውኃላ በተነሱ መምሕራን ያመኑ! " 》ምሳሌ ነው::
" የነሐሱ እባብ መሰቀሉ! " 《 ጌታም ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ! በመሰቀል የመሰቀሉ ምሳሌ ነው:: 》" አሰቃቀሉም እንደ ምን? ነው:: " ያልን እንደ ሆነ 《 በመካከል ቁሞ! + ከምድር ከፍ! + ከሰማይ ዝቅ! ብሎ! " ዐየር! " ላይ ሁኖ ተሰቅሏል! 》" በመካከል! " መሆኑ 《 እንዳስታረቀን ለማጠየቅ! 》 " መቆሙም! " 《 ምድርን በኪደተ እግሩ እንደ ቀደሰ! + እንደ ባረከ! ለማጠየቅ! 》 " ከምድር ከፍ! + ከሰማይ ዝቅ! " ብሎ " ዐየር! " ላይ መሆኑ " ዐየራትን ለመቀደስ ነው:: የቀደሙ ካህናት! + ነብያት! 《 ስብ አጢሰው! + ደም አፍሰው! 》 መስዋት ሰውተው ነበር እና 《 ዛሬ መስዋታችሁ ደረሰች! + ተፈፀመች! 》ሲል ነው::
《 ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተሰቀለበት መስቀል ከየት መጣ? 》 ያልን እንደ ሆነ ጥንተ ነገሩ እንዲህ ነው::
ሳኦል ልጁ ታመበት ጠቢባንን ሰብስቦ " ልጀን አድኑልኝ! " ቢል የማይቻል ሆነ " ምን ተሻለ! " ቢል " የገነት እጽ ቢገኝ ፈውስ ነበር! " አሉት:: " እሱማ የት?ሊገኝ? " ቢል 《 የንስር እንቁላል አምጠህ በግንብህ ዝጋበት እንቁላሉ ከዚያ እንዳለ ሲያውቅ "27፤ በአፍህ ትእዛዝ ንስር ከፍ ከፍ ይላልን? "
(መጽሐፈ ኢዮብ 39:27፤) እንዲል ከገነት እጽ ቆርጦ አምጦ ግንቡ ላይ ይጥለዋል "11፤ ንስር ጫጩቶቹን እንደሚያወጣ፥ "
(ኦሪት ዘዳግም 32:11፤) እንዲል ግንቡ ይሰነጠቃል! + እንቁላሉን ይዞ ይሄዳል! + ዕፁ ይቀራል! + በዚያ ልጅህ ይድናል ብለውታል! " 》ሳኦልም እንደ ተባለው አድርጎ ልጁ ተፈውሶለታል፠
ይህም ዕፅ 《 ገባሬ መንክራት! 》ነው:: በዮርዳኖስ ወንዝ ተክለውታል:: ሰለሞን ቤተ መቅደስ ሲሰራ አስቆርጦ አምጥቶታል መድረክ ሲያደርጉት አጥሮባቸው! + ቋሚ ሲያረጉት እረዝሞባቸው! + እንዳይቆርጡት አዝነው በደጅ ትተውታል:: ኃላም ንግስተ አዜብ " ታምሪን! " በሚባል ነገዴ እየተመራች ወደ ሰለሞን ጥበብን ልትፈትን "1፤ የሳባም ንግሥት በእግዚአብሔር ስም የወጣለትን የሰሎሞንን ዝና በሰማች ጊዜ በእንቆቅልሽ ትፈትነው ዘንድ መጣች።"
(መጽሐፈ ነገሥት ቀዳማዊ 10:1፤) እንዲል ስትመጣ ተረከዟ ላይ " እንደ ሚዳቋ ቀንድ! + የአህያ ሰኮናም! ሚመስል ይላሉ! " እሱ ነበረባት ይሄን ዕፅ ተረግጣ ስትገባ እንዳትታበይ ለምልክት እንደ ለምጽ ያለ ጥቁር ነጥብ ጥሎ አልፎ ውልቅ አርጎ ትቶላታል::
ኃላም " ሰለሞን! እና እሷ ንግስተ ሰባ! " አንድ! + አንድ! ብር እዋጠው አሽገውታል:: ይህም ስራአት ሁኖ ከእሱ ከሰለሞን በ
ውሀላ የተነሱት ነገስታት ሃያ ስምንት ናቸው ከሰሎሞን እና ከንግስተ አዜብ ጋር ሰላሳ ይሞላል ሲነግሱ አንድ አንድ ብር እያዋጡ አሽገውታል:: ኃላም አይሁድ ሰላሳውን ብር ለይሁዳ ሰጠው በዕፁ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ሰቅለውታል፠
አንድም ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን አይሁድ በጣም አርገው ይጠሉት ስለነበር መስቀሉን ሲሸከም እንዲከብደው ብለው
1《 ከመቃብረ አዳም የበቀለች ዕፅ አለች " ዕፀ ዘይት! " ትባላለች አንድ
2《 ሎት በእንባው ያለመለማት ዕፅ አለች ዕፅ ከርካ ሎሚ ትባላለች ሁለት
3《 ታቦተ ጽዮን ወደ ቅድስት አገራችን የመጣችበት ዕፅ አለች " ዕፀ ድንባዝ! " ትባላለች ሶስት
4 《 ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን በፍኖተ ቢታንያ የረገማት ዕፅ አለች " ዕፀ በለስ! " ትባላለች አራት
5 《 ዘኪዎስ የወጣባት ዕፅ አለች " ዕፀ ሰግላ! " ሾለ ትባላለች አምስት
እነዚህን ሁሉ ካንድ አርገው አስተባብረው ሰቅለውታል::
ይህ " ነገረ መስቀል! " እንዴት መጣ ያልን እንደ ሆነም
《 በእሱ መከራ ስጋ! + እኛ ከመከራ ነፍስ ድነናል! 》 እንዲል《 ይህንንም መከራ " ነገረ መስቀል! " " ሔዋን! " በአምስት በኩል አምጣዋለች::
በዐይና አይታ! +
በጀሮዋ ሰምታ! +
በእግራ ሂዳ! +
በእጅዋ ቆርጣ! +
በአፍዋ በልታ!
እሱም 《 ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ በዚህ ሁሉ ክሶልናል! 》
በጀሮው " የአይሁድን ዘለፋ ሰምቷል! " +
በዐይኑ " ግርማ አይሁድን አይቷል! " +
እጁን! + እግሩን! " ተቸንክሯል! " +
በአፉ! " መራራ ሐሞትን ቀምሷል! "
በእሱም ሞት
《 ወደ ነፍሳችን እረኛ ወደ ጠባቂያችን ተመልሰናል! 》
"25፤ በመገረፉ ቁስል ተፈወሳችሁ። እንደ በጎች ትቅበዘበዙ ነበርና፥ አሁን ግን ወደ ነፍሳችሁ እረኛና ጠባቂ ተመልሳችኋል።"
(1ኛ የጴጥሮስ መልእክት 2:25፤) እንዲል!
" እንደ በጎች ትቅበዘበዙ ነበር! " አለ 《 እንደ ታመመ በግ! 》 ማለት ነው:: የተመመን በግ ከመጋው ለይተው! + ከደረቅ ቦታ አስረው! + ደረቅ ሣር! + ጥሩ ውኃ ይመግቡታል! + ሲድን ታቅፈው ቀስደው ከመንጋው ይጨምሩታል:: " እንደ ታመመ በግ! " አለ 《 " ታሞ! " የነበረ ገነትን ያህል ቦታ! + እግዚአብሔርን ያህል ጌታ! አጦ የነበረ " አዳም! " ነው:: " 》" ከመንጋው እንደ መለየት! " 《 አዳምም ከማኅበረ መላእክት ተለይቷል! 》" ከደረቅ ቦታ አስረው! + ደረቅ ሣር! + ጥሩ ውኃ! እንዲመግቡት! " 《 ነፍሶሙሰ ለጻድቃን ውስተ እደ እግዚአብሔር ወኢለከፎሙ ላህበ ሥቃይ ወኢምንትኒ! 》 እንዲል《 5500 ዘመን በእደ እግዚአብሔር ሲጠበቅ ኑሯል! 》" ሲድን ወስደው ከመንጋው እንዲጨምሩት! " 《 ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስም ባሕርዩን በሕርይ አድርጎ! + ጽንዓ ነፍስን ሰጥቶ አድኖታል! 》
《 መስቀሉ ሰባት ክንድ ነው! 》
" ከፍልፍሉ! " የገባው አንድ ክንድ ከስንዝር! +
" ከእግሩ በታች! " ያለው አንድ ክንድ! +
" የተሰቀለበት! " ሶስት ክንድ ከስንዝር! +
" ከራሱ በላይ! " ያለው አንድ ክንድ!
አጠቃላይ " ሰባት ክንድ! "
《 ወስብሐት ለእግዚአብሔር! 》

Comments
Post a Comment