ሩሲያ እና ኦርቶዶክስ ሃይማኖት
ዳዊት ፀሐይ
በ10ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ከባይዛንቲየም ሚስዮናውያን የተቀየሩት ልዑል ቭላድሚር ቀዳማዊ ክርስትናን የሩስያ ሕጋዊ ሃይማኖት አድርጎ ተቀበለ። ከዚያም ለ1,000 ለሚጠጉ ዓመታት ያህል የሩሲያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን የአገሪቱ ዋነኛ ሃይማኖታዊ ተቋም ሆነ። ከእዛ በ1917 ኮሚኒስቶች ሥልጣን ከያዙ በኋላ የሃይማኖት ተቋማት ተጎዱ። የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን አብዛኛውን ንብረቷን ለመውረስ ተገደደች። ብዙ መነኮሳት ከገዳማቸው ተፈናቀሉ። የቀድሞዋ ሶቪየት ኅብረት ሕገ መንግሥት የሃይማኖት ነፃነትን በስም የተረጋገጠ ቢሆንም ኦርቶዶክሳዊ ሃይማኖታዊ እንቅስቃሴዎች በጣም ይገድብ ነበር። እናም ኦርቶዶክሳዊ ሃይማኖተኛ መሆን ከኮሚኒስት ፓርቲ አባልነት ጋር እንደማይጣጣም ይቆጠር ነበር። ስለዚህም ግልጽ የሆነ የኦርቶዶክስ ሃይማኖት አማኝ መሆን ለግለሰብ እድገት እንቅፋት መሆነ ጀመረ። በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወቅት መንግሥት ከፋሺዝም ጋር በሚደረገው ውጊያ የክርስቲያኖችን እና የአይሁዶችን ድጋፍ በሚፈልግበት ጊዜ የኦርቶዶክስ ክርስትና እምነት ተከታይ የሆነ ማንኛውም ግለሰብ እምነቱን በፈለገው መንገድ መግለጽ ይችላል በማለት ፈቀደ። ከእዛ ጦርነቱ ሲያበቃ እንደገና በኦርቶዶክክ ሃይማኖት ላይ ተመልሶ እገዳ መጣል ጀመረ።
እ.ኤ.አ. በ 1980 ዎቹ በ Mikhail Gorbachev የለውጥ አራማጅ አገዛዝ ፣ " a policy of glasnost " የግላኖስት ፖሊሲ (“ክፍትነት”) ወይም የሃይማኖት ነጻነት ታወጀ። ይህም የሃይማኖት አዋጅ የበለጠ መቻቻልን አመጣ።
ከዚያ በኋላ ማለትም ከሶቪየት ኅብረት መፍረስ በውኃላ የኦርቶዶክስ ሃይማኖት ነፃነትን እውን ያደረገ እና በርካታ የሕብረተሰብ ክፍሎች የተለያዩ እምነቶችን መከተል እንዲችሉ አድርጓል። በእርግጥም ከ1990ዎቹ ጀምሮ ብቅ ያሉት የሩሲያ ብሔርተኞች የሩስያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያንን እንደ ሩሲያ ባህል ዋና አካል እንደሆነች ለይተው አውቀዋል። ለይተዋል።
ዛሬ የሩሲያ ኦርቶዶክስ የሀገሪቱ ትልቁ ሃይማኖት ነው። በ20ኛው መቶ ክፍለ ዘመን አብዛኞቹ የሶቪየት ኅብረት ባለስልጣናት ሃይማኖት ስለሌላቸው በተደራጀ አሠራር የኦርቶዶክስን ሃይማኖት በመጨቆናቸው ምክንያት ሃይማኖት የሌላቸው ሰዎች ዛሬም በሩስያ አሉ። ከህዝቡ አንድ አራተኛው የሚይዙት እነሱ ናቸው። ይሄም ማለት ኦርቶዶክስ ሃይማኖት 53% ስትይዝ ሃይማኖት የሌላቸው ሰዎች 27% ድርሻ አላቸው። በጣም ትልቅ ቁጥር ነው። እስልምና የሩሲያ ሁለተኛው ትልቁ የሃይማኖት ክንፍ ነው። ሌሎች የክርስቲያን ቤተ እምነቶች በጣም ያነሱ ሲሆኑ በ17ኛው ክፍለ ዘመን ከሩሲያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን የተለዩትን የብሉይ አማኞች እና የባፕቲስት እና የወንጌላውያን ቡድኖች በ20ኛው ክፍለ ዘመን በአባልነት በመጠኑ ያደጉ ናቸው።
በ1997 ከአምስት ነባር ሃይማኖቶች ውጭ ያሉ ቤተ እምነቶችን የሚገድብ ሕግ ወጣ። እነሱም የሩሲያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ፣ እስልምና፣ ይሁዲነት ፥ ቡዲዝም እና ፕሮቴስታዚም ነው። ሕጉ በሥራ ላይ በዋለበት ወቅት ይህንን መስፈርት ያላሟሉ ቡድኖች (እንደ ሮማን ካቶሊኮች እና ሞርሞኖች) የትምህርት ተቋማትን መሥራት ወይም ሃይማኖታዊ ጽሑፎችን ማሰራጨት አልቻሉም። ሌሎች ግን ችለዋል።
Comments
Post a Comment